የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ጽ/ቤትን በአዲስ መልክ ለማስገንባት ከአማካሪ ድርጅት ጋር ውል ተፈራረመ፡፡

Share Article

መጋቢት 21/2018 ዓ.ም- አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ጽፈት ቤትን በአዲስ መልክ ለማስገንባት በርካታ የቅድመዝግጅት ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ የቅድመዝግጅት ሥራዎቹ አንድ አካል የሆነውን የአማካሪ ድርጅት ውልም ስታዲያ የምህድስና ሥራዎች አማካሪ ኃላፊነቱ የተወሰኑ የግል ማህበር ከተሰኘ ድርጅት ጋር በዛሬው ዕለት በዋናው መሥሪያ ቤት ተፈራርሟል፡፡

የባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን መኮንን እና የስታዲያ የምህድስና ሥራዎች አማካሪ ኃላፊነቱ የተወሰኑ የግል ማህበር ተወካይ ኢንጂነር አበራ አበበ ውሉን የተፈራረሙ ሲሆን ድርጀቱ ቃሉን ጠብቆ የባሌ ታሮች ብሔራዊ ፓርክ አሁን ያለበትን ደረጃ የሚመጥን የጽፈት ቤት ግንባታ በሚገነባበት ሒደት ዙሪያ ከባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ጋር የገባውን ሥምምነት እንዲያከብር የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን መኮንን አሳስበዋል፡፡

የስታዲያ የምህድስና ሥራዎች አማካሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ተወካይ ኢንጂነር አበራ አበበም ከኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ጋር አብሮ ለመሥራት ከሥምምነት መድረሳቸው ለድርጅታቸው ኩራት መሆኑን ገልፀው ድርጅታቸው በገባው ውል መሠረት ጥራቱን የጠበቀ እና አሁን የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ያለበትን ደረጃ የሚመጥን ጽ/ቤት በሚገነባበትት ሂደት ዙሪያ በኃላፊነት እንደሚሠራ በድርጅቱ ሥም ቃል ገብተዋል፡፡

ኢዱጥባ

Recent News