የቱሪዝም ዘርፍ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር የሪፎርም ዝግጅት ምዕራፍ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ፡፡

Share Article

መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም

በቱሪዝም ዘርፍ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ዐቢይና ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በዘርፉ እያከናወኑት ያለውን የሪፎርም ዝግጅት ምዕራፍ አፈፃፀም በመገምገም የቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።

በመድረኩ የሪፎርሙ የቴክኒክና የንዑሳን ኮሚቴዎች አጠቃላይ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ የዝግጅት ምዕራፉ የደረሰበት ደረጃ፣ የተመዘገቡ ውጤቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ ዝርዝር ውይይት ተካሂዷል።

በተለይም የዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ታስበው እየተከናወኑ ባሉ የፖሊሲና የሕግ ማዕቀፎች፣ የመንግስት አገልግሎት ስነ-ምድብ (Service Taxonomy)፣ የሙያ ምደባ፣ አደረጃጀትና የብቃት ማዕቀፍ ላይ ሰፊ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን፤ ከዚህ በተጨማሪም ነጻና ገለልተኛና እንዲሁም አካታች ብዝሃነትን የሚያስተናግድ ተቋማትን መፍጠር፤ የሠራተኞች ስምሪት እንዲሁም የመንግስት አገልግሎትና የሠራተኞች ስምሪት ኦዲትና ቁጥጥር ሥርዓት፣ አስተዳደራዊ የሪፎርም ጉዳዮች እንዲሁም ኮሙኒኬሽንና ዲጂታላይዜሽን ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ተደርጓል።

የቱሪዝም ሚኒስትር ክብርት ሰላማዊት ካሳ መንግስት ለሪፎርሙ ከሰጠው ከፍተኛ ትኩረትና ፋይዳ አንጻር የቴክኒክና የንዑሳን ኮሚቴዎች የጀመሯቸውን ሥራዎች አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል። በመጨረሻም ሊስተካከሉና ሊካተቱ የሚገባቸው ሃሳቦች በአጭር ጊዜ ውስጥ ተሟልተው ለውሳኔ እንዲቀርቡ አቅጣጫ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።

ቱሪዝም ሚኒስቴር

Recent News